Open Studio
MP3

Free to use on YouTube, TikTok, Reels — no Content ID claims. Tag @starsinger.ai when you do.

የስያሜ ሚዛን

Creator
@lucid_quasar_11
Reggae / Dancehall3:30October 2, 2026
0:00 3:30

Lyrics

ሀገሬ ቅኔዬ ሰምና ወርቅሽን በተግባርሽ አውሪ
እስቲ ላንዴ አድምጭኝ ለልጅሽ ተጠሪ
ተቀመጪ ስሚኝ ከፍርድ ሸንጎዬ
ተከሳሽም ዳኛም አንቺ ነሽ እምዬ
ስያሜ ነው ክሴ ካንቺ ጋር በኖርኩት በትንሹ እድሜዬ

ከተግባር ሚዋደድ ባልሆን ስም ቀማሪ
ቅር ይልሽ ይሆን ወይ
በዚህ ብሰይምሽ እንዲህ ብትጠሪ
ከበዙ ስሞችሽ የሚገልጽ ስምሽን
ልቆ የሚመዝን ከስያሜ ሚዛን
ከስሞችሽ መሐል ስምሽ የቱ ይሆን?

አንቺ የገዢዎች ግዙ
የጌታ መጋዣ የጪሰኛ ወዙ
በዘመን እርጅና እድሜ ጠገብ ኗሪ
ከባላባት ቤት ስር የባርያ ቀባሪ
የዘመን አንቡላ የታሪክ ቅራሪ
የደም አኬልዳማ ነፍስ በልቶ አዳሪ
የምስኪናን እምባ ንፁህ ምታጎድፊ
የገዳዮች ምድር ስለታም ቀጣፊ

የማልገራሽ ፈረስ የማትቆሚ ጅረት
ጊዜ ማያርምሽ የማትጠግቢ ሞት
በአልቃሾችሽ እምባ ደጅሽን ምታጥቢ
ልጆችህን ማግረሽ ቤት ምትገነቢ
ጠላት ልታኖሪ ጠላት ልታስገቢ

ሀገሬ ቅኔዬ ሰምና ወርቅሽን በተግባርሽ አውሪ
እስቲ ላንዴ አድምጭኝ ለልጅሽ ተጠሪ
ተቀመጪ ስሚኝ ከፍርድ ሸንጎዬ
ተከሳሽም ዳኛም አንቺ ነሽ እምዬ
ስያሜ ነው ክሴ ካንቺ ጋር በኖርኩት በትንሹ እድሜዬ

ከተግባር ሚዋደድ ባልሆን ስም ቀማሪ
ቅር ይልሽ ይሆን ወይ
በዚህ ብሰይምሽ እንዲህ ብትጠሪ
ከበዙ ስሞችሽ የሚገልጽ ስምሽን
ልቆ የሚመዝን ከስያሜ ሚዛን
ከስሞችሽ መሐል ስምሽ የቱ ይሆን?

አንቺ የሐሰት ሹመኛ መቀመጫ መንበር
የጉልበተኞች የባለጡጫ ፈር
ስለእውነት ኗሪንምታለብሺ አፈር
የፌዘኛ ዜማ የቧልተኛ ምድር

አንቺ ባልሽን ምትገፊ ለውሽማሽ ድሎት
ልጆችን የሰረቅሽ ከልጆችሽ አባት
የሐቀኛ ዕምባ የደም አፍሳሽ መሬት
እውነት ስምሽ ማነው አንቺን ሚጠሩበት

አንቺ የእምነት ጥላሸት የክህደት ማኖርያ
የቀማኛ ደስታ የነጣቂ ወኔ የትዕቢት ማጎርያ
የፃድቅ ገሃነም የሃጥዕ አለሙ የፍርድ ማጣመምያ
ሀገሬ ቅኔዬ ሰምና ወርቅሽን በተግባርሽ አውሪ
እስቲ ላንዴ አድምጭኝ ለልጅሽ ተጠሪ
ተቀመጪ ስሚኝ ከፍርድ ሸንጎዬ
ተከሳሽም ዳኛም አንቺ ነሽ እምዬ
ስያሜ ነው ክሴ ካንቺ ጋር በኖርኩት በትንሹ እድሜዬ

ከተግባር ሚዋደድ ባልሆን ስም ቀማሪ
ቅር ይልሽ ይሆን ወይ
በዚህ ብሰይምሽ እንዲህ ብትጠሪ
ከበዙ ስሞችሽ የሚገልጽ ስምሽን
ልቆ የሚመዝን ከስያሜ ሚዛን
ከስሞችሽ መሐል ስምሽ የቱ ይሆን?

Want to make Reggae / Dancehall yourself? See how Star Singer compares to Suno and Udio for AI Reggae / Dancehall generation.

Make a Reggae / Dancehall like this with AI

Generate your own AI Reggae / Dancehall song in 90 seconds — first one free, full commercial rights, vertical music video included.

Make an AI Reggae / Dancehall song → Open Studio

FAQ

Who made "የስያሜ ሚዛን"?

"የስያሜ ሚዛን" was made by @lucid_quasar_11 on Star Singer, where anyone can write and sing an original song with AI.

What genre is የስያሜ ሚዛን?

የስያሜ ሚዛን is Reggae / Dancehall.

Can I listen to "የስያሜ ሚዛን" for free?

Yes. "የስያሜ ሚዛን" streams free on Star Singer — no subscription required. You can also make your own: one AI song a day is free, extra songs with a lyric video are $1.99, a lip-synced music video starring you is $19.99, and cinematic videos start at $2.99.

Can I create my own AI song?

Yes. Star Singer lets you create AI-generated songs and music videos. Clone your voice, pick any style, and generate original music. Listening is free and unlimited, and one song a day is free to make — no subscription.

Make an AI Reggae / Dancehall song →